Tumgik
selehadinali · 2 years
Photo
ለሀዘን መወድስ
አይኗ - የተዘጋ መጻፍ
ልቧ - የተዘጋ በራፍ
ብትጽፍ - የሀዘን ሙዚቃ
ኑረዋለች መሰል እርሷ እንዲህ ናት በቃ ::
አለ አይደል
ሳይገሉ እንደ መግደል
ሰባብሯት ተለየ - አረገበው ክንፏን
የተወላት ነገር ብዕርና መዳፏን ::
እነሆ መወድስ ስላለባት ሃዘን
ሀቅ ጋር ያደርሳል ተጥዶ መመዘን
የጫረችው ሞልቷል - ትኖረው ምን የላት
መሳታወሻዋን እይ - የደም ገንቦ ቃላት
ሀዘን ሀዘን ሀዘን - ሀዘን ቢወራላት ::
Tumblr media
95 notes · View notes
selehadinali · 2 years
Photo
ሦስት ጥያቄዎች
እርሷን ማፍቀር እንዴት ነበር ? ጠየቀኝ ምስጋና :-
' ከተደፈነብኝ ጉድጏድ ቀድጄ እንደ መውጣት ነው ' እኔም መለስኩ - ' ባንዲት የጮራ ዘንግ ወደ ህይወት እንደ መምጣት :: '
በእርሷስ መፈቀር እንዴት ይሆን ? ጠየቀኝ ደስታ ::
መለስኩኝ :- ' ለዓመታት በጨለመ ምድር ውስጥ እንደ መታየት ፥ ከእድሜ ልክ ዝምታ በኇላ እንደ መሰማት ያለ ነው :: '
እርሷንስ ማጣት እንዴት ይሆን ? ጠየቀኝ ሀዘን ::
ከረዥም ዝምታ በኇላ መለስኩኝ :-
'በህይወቴ የተባልኳቸው 'ደህና ሰንብት'ቶችን ሁሉ በአንድ ቃል ድጋሜ እንደ መስማት ነው :: '
-
Lang Leav
Tumblr media
62 notes · View notes
selehadinali · 2 years
Photo
Tumblr media
62 notes · View notes
selehadinali · 2 years
Text
لي كان ظل رسوم فاستوت شمسي فزالا
عشت بالمحبوب حقاً بعد ما كنت خيالاً
عاد محبوبي وجودي فتجلى وتعالى
وتخفى عن عياني بي عِزا وجلالا
حبذا سلبي ووجدي فيه حالا ومالا
لست أخشى بعد هذا منه والله انفصالا
كل أحوالي فيه فرحات تتوالى
هكذا العشق والا كان والله افتعالا
يا مفيد الغصن ليناً وانعطافاً واعتدالا
أنا في عين التجني أجتني منك وصالا
يا معير البدر أنسا وضياء وكمالا
أنت في طرفي وقلبي ساكن تأبى أنتقالا
يا حياة الحي عزا وغناءً وجمالا
لم يزل روحي وراحي فيك لطفاً ودلالا
كلما شاهدت حبي من محياك مثالا
علمت عيناه فكري يعمل السحر الحلالا
وتملا بك قلبي فيه لا أخشى ملالا
ووفا مبلغ قصدي في الرضا حالا و
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
ዓለም ሆይ !
አንድ ቃል አለኝ
በዝምታሽ ውስጥ ቋጥረሽው ይቅር
ወግ ደርሶኝ ሙቼ ስቀበር :-
" እኔም አፍቅሬ ነበር ! "
[ Rabindranath Tagore ]
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
A Valediction Forbidding Mourning
By John Donne (1572–1631)
AS virtuous men pass mildly away,
And whisper to their souls to go,
Whilst some of their sad friends do say,
‘Now his breath goes,’ and some say ‘No’;
So let us meet and make no noise, 5
No tear-floods, nor sigh-tempests move,
’Twere profanation of our joys,
To tell the laity our love.
Moving of th’ Earth brings harm and fears,
Men reckon what it did and meant; 10
But trepidation of the spheres,
Though greater far, is innocent.
Dull sublunary lovers’ love,
(Whose soul is sense) cannot admit
Of absence, ’cause it doth remove 15
The thing which elemented it.
But we by a love so far refin’d,
That ourselves know not what it is,
Inter-assured of the mind,
Careless eyes, lips, and hands, to miss; 20
Our two souls therefore, which are one,
Though I must go, endure not yet
A breach, but an expansion,
Like gold to airy thinness beat.
If they be two, they are two so 25
As stiff twin compasses are two,
Thy soul, the fix’d foot, makes no show
To move, but doth, if th’ other do.
And though it in the centre sit,
Yet when the other far doth roam, 30
It leans and hearkens after it,
And grows erect as that comes home.
Such wilt thou be to me, who must
Like th’ other foot, obliquely run,
Thy firmness makes my circle just, 35
And makes me end where I begun.
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
Tumblr media
“Remembering, I sigh; looking ahead, I sigh once more : This life is mist . What fame? What glory?”
— Li Po
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
Tumblr media
አንዳንችን ላንዳችን እንደ እህት ወይም እንደ አንደ አንድ አሪፍ ጎረቤት ነን እኛ ዛፎች - ለዛፎች :: ለታናናሾቻችን ማዘን አለን ጥላ ሲፈልጉ ዘመም እንላለን :: ብቸኛ ሲሆኑ ወፎች እንልካለን በውድቅት ሌሊት - ቢያጫውቷቸው :: ወቅት ሲያስውበን አንዱ ያዱን ፍሬ ለመንጠቅ ወደ ሌላ ዛፍ እጁን አይሰድም ፤ አንዱ ቀድሞን በድርቅ ቢመታ ሳቅ አይቀድመንም ::
ምክናያቱም እኛ ዛፎች ፍፁም ከዛፍ ቆራጩ እንለያለን :: ቆራርጠው ጀልባ አርገው ሲሰሩን መዋኘት እንማራለን :: የቤት በር ሲያደርጉን ምስጢር እንጠብቃለን ::
ዛፍ ወንበር አድርገው ቢሰሩት እንኳ ፥ በሆነ ወቅት ከበላዩ የነበረውን ሰማይ አይረሳም ። ጠረጴዛ ቢያደርኩት አናቱ ላይ ተደፍቶ የሚፅፍን ገጣሚ ዛፍ ቆራጭ እንዲሆን አያስተምረውም ::
ዛፍነት ይቅርታ ፣ የበረታ ጥንቁቅነት ማለት ነው :: ዛፍ አይተኛም አያንቀላፋም ፤ ግን ለህልመኞች ሀቁን አሳልፎ ይሰጣል ፤ በቀንም በሌሊት ጠባቂ ዘብ ነው ፤ ላልፎ ሂያጅ እገረኛ ከፍ ላለው ለሰማዩም ክብር አለው ። ዛፍነት የቁም ፀሎት ፤ በምልዐት መሰጠቱን ወደ ሰማይ አምዘግዝጎ መላክ ። ሞገድ ከዳበሰው በስሱ ራሱ ቢታጠፍ በክብር ነው ጎንበስ የሚለው - እንደ መኖክሲት - ግን ዘለለቷን ቀና እያለች የበላዩን እንደምትፈገው ሁሉ ::
ባላፈው ገጣሚው 'ምናለባት ወጣቶች እንደ ድንጋይ ቢሆኑ ኖሮ ' አለ ፤ እኔም እላለሁ ' ምናልባት ወጣቶች እንደ ዛፍ ቢሆኑ ኖሮ ' ::
[ ሀሳቡ - የ Mahmoud Darwish ]
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
Tumblr media
በአድማስ ደማስ መፍሰስ ያውቅሽበት - አንቺ ፤ በመሬት ፅዋ-ተርታ ፥ እያጓራሁ የምረታ - እኔ ። ደግሞ ዜማ አለሽ በውል - ሰማያዊ ፤ ላንቺ ዝቅ ዝቅ ዝቅ ብል ምኔ ሊጎድል ?!
Nothing is so strong as gentleness,
and nothing is so gentle as true strength.
~ Ralph Sockman
[Image: Everything_except_colorful]
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
"ዋሪዳ ተቀባዩ - አባ መውደድ"
-
ስድስት መፅሀፍ ሆነው የዘለቁትን የስንኞች ጎርፍ ፥ ዘመነኞቹ ሲያጠኑት የመጀመሪያው ቅፅ ሲጀምር የምናገኘው ታሪክ [ብኩይ የዱር - መቃ እንጉርጉሮ ወይም Song of the Reed ] ፥ ከስድስተኛው ቅፅ መጨረሻ ላይ ከምናገኘው ቅኔ - ለበስ ዜማዊ ተረክ ጋር ሆነ ብለው በማጋመድ የቋጩት ይመስላል ይላሉ ። [Song of the Reed ን ጊዜ ካለን እንደ ገንቦ ሁሉ በውስጡ ያለውን የብርሀን ወይን ለማፈንዳት ፥ በተመስጦ ጦር መንደላችን አይቀርም ... ] ኪታቦቹ መስናዊ (መስናቪ) ፥ ዋሪዳ ተቀባዩ አባ - መውደድ ፥ ህልመኛው መውላና ጀላሉዲን ሙሀመድ ሩሚ !
ጥናቱን ከፍ አድርገው Seyed Safavi and Simon Weightman ፥ ሩሚ መፅሀፉን በምልዐት ሲሰፋው በጥብቅ ጥንቃቄ ነበር ይላሉ ፥ ለዛም ነው ቀልበት - አስተኔ መልክ ይዞ የምናገኘው [Masnavi as a whole was carefully designed by Rumi using ring composition .]
" እና ?"
እናማ ልሙጥ ውብ ቀለበት እያገላበጥን ከጣታችን ብናጠልቀው ፥ ውበቱ አይጎድል ፥ ስህተትም ነው አይባልም
" እና ?"
እናማ የሳቸው ስልቱ ይመቻል ፥ ያሻው ከእልፍ ገፆች - ከመስናዊ ፣ እኩሉ ከጥቂት ምዕራፎች ከመስናቪ ፣ የፈለገም ከአንዲት ገፅም ወይም ከአንዲት መስመር ጋር ጥንቅንቅ መግጠም ይችላል ።
ለሳቸው 'ቁርአን' እንደ ተምሳሌታዊው የKing Jamshed ጎድጓዳ ገበቴ[a proverbial bowl of the legendary king Jamshed ] የአለም የአፅናፍ ድምር ፥ የንጋት የሌት ድውር ፥ ርቀቱን ልህቀቱን ያይበት ነበር እንደሚባለው ሁሉ ፤ ቁጥር አለፍ የዋሪዳና የተመስጦ ከፍታቸው ላይ እንዲወጡ የሀሳብ እና የከፍታ መንገድ ሆኖ አልፏል ። [እኔም እስካሁን አንድ መስመር አድርገው ከሰፏት ስንኝ ጋር በፍቅር እንደወደኩ አለሁ ፥ ኢንሻአላህ በሌላ ወግ እንመጣለን ]
በጋሊብ በተሰናኘ ግሩም ሀሳብ [በውብ ግጥሙ ] ፥ ልናያቸው እንሞክረና ከመስናዊ ባገኘናት ወግ እናሳርጋለን [አንድ ሰው ከገንቦው እንዳሰፋፈሩ ብለን የለ ]
There is no dearth of poets
but not all poets are the same.
There are some who are drunk
with the commonplace wine.
There are those who mix in their drink
saqi’s beautiful glances.
But let us admit that
there are those who have something unique.
Their work can’t be described with a label like poetry because it is limiting.
What is beyond poetry is indescribable—
deep beauty for which no words exist
[ እንደኔም ገጣሚዎች ወላ ባለ ቅኔዎች ውብ ናቸው ከምር ከምር ሲሆን ከሰገነት ማውረድ አይቻልም - ምናባቸውን ! ፥ ሁሉም አቻ ባይሆኑም አንዳንዶቹ ከአንድ ኩስኩስት የዋሪዳ ወይን ይጠጣሉ ፥ ሌሎች ከአሳላፊው ውብ ግርምምታ (ከአይኑ መቃድ ጋር የውበትን መልክ ስሎ) ጋር የመሚጎነጩ አሉ ። ሌሎቹ ግን ሩቅ የማይገለፀውን ቃለ - አልቦ ጥልቀ - ውበትን የሚስሉ በአስማታዊ ብዕራቸው ]
ሩሚን ከመጨረሻዎቹ እንደሚሰለፉ እናምናለን ፥ ባለ ቅኔዎች ሁሉ የውበትን ንዝረት ፥ ድንገቴ እርምጃ ፥ የተፈጥሮን ረቂቅ መስህብ ፥ ያልተበጣ የሳቅና የሀዘን ስብ ለመብጣት ሲተጉ የሚጓዙት ወደ ማይታወቀው ነው እርምጃቸው ፥ ጉዟቸው ፤ ሀያሲው Hali ' Journey to unknown' እንደሚለው
ሁሉም ግን ናፍቆት ይሰፍራል ፥ ከዚሁ ከ ለት - ተለት ሩጫው ጋብ ሲል ፣ ሁሉም ሀዘን ይሰፍራል ያለበትን ሁኔታ ልብ ሲል ፣ ሁሉም ውስጡ ሙሾ አያጣም ከድብቅ አለም ጥሪ የሚነሳ !
ከፍ ከፍ ሲል ገጣሚ ይሄን ይገልፀዋል - ለጊዜው በምን እንረፍ ስንል - ከሩሚ ሁለተኛው ቅፅ ላይ የ Chinese and Greek Painters ታሪክ እናገኛለን ...
"ሁሉቱም ታላቅ ህዝቦች ነን ይሉ ነበር - በዘመናቸው ። አንድ ታላቅ ሱልጣን ክርክሩ ጋብ ቢል በማለት ፥ ከሀገሩ ከሚገኙ ትላልቅ ትይዩ ግድግዳዎች ላይ የስዕል ውድድር እንዲያደርጉ ይጋብዛል ።
ቻይናዊያን ቀድመው አስፈላጊውን ቁሳቁስ ሁሉ ወሰዱ መዓት ጓዝ ፤ ግሪካዊያን ጥቂት እቃዎች - ሱልጣኑ እስኪገረም የፅዳት ቁሳቁስ ብቻ ። መጋረጃ በሁለቱ ግድጋዳዎች መሀል ተደረገ ግሪካዊያን ከወዲህ ቻናዊያን ከወዲያ
ቻናውያን ያላቸውን ጥበብ ሁሉ ተጠቀሙ ፥ ግድግዳውን ጉድ ባሰኘ ስዕል ሞሉት ። ግሪካዊያን ከወዲያ ለፅዳት በሚውል ልዩ ድንጋይ ተጠቅመው ከድግዳው ላይ ያለውን ለአመታት የተረሳውን ፥ እድፍ እና አሰር ሁሉ አፀዱ - ብለልጠታቸው ቻይናዊያን ምን እንደሚስሉ ያውቁ ነበር።
ከሰዓታት በኋላ ቻናዊያን መጨረሳቸው ተበሰረ ንጉስ መጣ ፥ ህዝብ ተሰበሰበ ... በህይወቱ አይቶት የማያውቀውን ውበት በጥበብ ከተሰራው የቻይናዊያን ግድግዳ ላይ ያስተውላል
ግሪካውያንም መጨረሳቸው ሲታወቅ በሁለቱ መሀል ያለው መጋረጃ ይከፈትና ወደ ሁለተኛው ስራ ይዞራል ፥ ከድሮው የቀረ ምንም አይነት እድፍ የለም ሁሉም በጥንቃቄ ተወግዷል - የሚገርመው የቻያናዊያኑ የጥበብ ስራ ከነ ሙሉ ሞገሱ ፥ ከነ ሙሉ ውበቱ ከዚህኛው ግድግዳ ላይ ይንፀባረቅ ነበር [The work of the chinese painters ,in all its complexity and beauty , was manifested in the art of the Greek painters' simplicity and transparency , thus rendering it unfathomably more glorious].
በፅዱ ግድግዳቸው ዳግም ውበት መፍጠራቸው ግሪካዊያኑ ፥ ንጉሱን ሁሌ ሲያስገርሙ ኖረ ይሉና ..
የኛም ጉዞ በዚህ ይመሰላል - ስለዚህ የልብህን ጥግ ወልውል በውል - ያኔ Divine beauty ባንተ መንፀባረቁ አየይቀርም " በማለት ይጨርሳሉ
መልካም ጁምዓ
Tumblr media
1 note · View note
selehadinali · 2 years
Text
፩ .
የግመሏ ልጅ እናቱን " እማዬ ይሄን ሁሉ መንገድ ተጓዝሽኮ ለምን አረፍ አትዪም ? " ብሎ ሲጠይቃት
" ልጄ ሆይ ልጓሙ በጄ ቢሆን ኖሮ ፥ ሸክሙንም አታይብኝ ፣ ከቅፍለቱ ሰንሰለት ውስጥ አታገኘኝ ፤ አሳዳሪያችንም ቢፈልጉኝም አያየጉኝም ነበር "
Fate is the helmsan of the ship of life , no matter though the owner rend his clothes.
O, Sa'di !
፪ . በሆነ ምሽት ፥
"በራሪ ብራ - ተኩስ(firefly) በአፀደ - ፅጌያት ውስጥ ልብ ብለህ ይሆናል" ይላሉ ሰዓዲ ሺራዚ ፤ ይቀጥሉና ፥ " አንድ ሰው ብራ - ተኩሷን ' አንቺ ብናኝ ፥ የሌት መናኝ ነቁጥ ብርሃን ፤ በቀን በቀን ምነው የማናይሽ ? ' በማለት ይጠይቃታል"
" እርሷም ድንቅ የጠቢብ መልስ ፈለቃት :- ' እኔኮ ከፀሀይ ፊት ስቆም የምንም ያክል ነው ቦታዬ ! ' "
፫. ሰዓዲ ሺራዚ እንዲህ ይላሉ ፦
" ተማሪ እያለሁ ፥ ለኔ ጥሩ ስሜት የሌለው ልጅ እንዳለ ልብ አልኩና ፥ ለሼይኻችን ' መምህር ሆይ ለጥያቄዎት አምረቂ መልስ ሳቀርብ ፥ ከወዲያ ያለው ልጅ በቅናት ፊቱ ሲለዋወጥ አያለሁ ' አልኳቸው
ድንቅ መልስ አቀበሉኝ ፦ " ምናልባት ጓደኛህ በክፉ የሚቀናብህ ከሆነ ስህተት ሊሆን ይችላል ፤ አንተ ግን አሱን ልታማ እና በይፋ ስለሱ ልታወራ ማን ፈቀደልህ ? አንዱ በቅናት መንገድ ወደ ስህተት የተጓዘ እንደሆን ፥ ያንተ ገመናን እያወሩ በስህተት መከተል ምን ይሉታል ? "
If he seeks perdition through the path envey , thou wilt join him by the path of slander
[- The Orchard Of Sa'di - ምንጭ ]
መልካም ጁምዓ
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
ነገረ - ፍቅር
፩.
"በሆነ ወቅት ባህላዊ ጨዋታ በሚጫወቱ ወጣቶች መሀል አለፍኩ ይላሉ " ሰዓዲ አል - ሺራዚ ። "አንድ ብላቴና ሲዘፍን ፥ አንዷ ወጣት ረቅስ(ዳንስ) ለመጫወት ተነሳች ፥ በመሀል ልብሷ ከሻማጋ ተገናኝቶ ኖሮ መቀጣጠል ይጀምራል በስሱ - ልብም ያላት ግን የለ ። ልጅቷ ተናደደች ፣ ተካፋችም "
" ከወደ መጨረሻ ጥጉን ይዞ የተቀመጠ አንድ ወጣት አፍቃሪ ልጅ ብቻ ፥ እንዲህ ሲል ተናገራት " ፦
ስለምን ልብሴ ተቃጠለ ብለሽ ትቆጫለስ ፣ እኔን ሚንቀለቀለው የእሳት ቋያ የህይወቴን አዝመራ አጥፍቶት የለምን ?!
Why agitate thyself ? The fire has burned thy skirts - it has entirely consumed the harvest of my life .
፪. ይቀጥሉ ሰዓዲ
እኩለ ሌሊት ነው ፥ እንቅልፍ አልነበረኝም ፤ እሰማለሁ የ'ሳት እራት ከሻማዋ ጋር ወግ ይዘዋል ።
" እኔ አፍቃሪህ ነኝ ፥ ብቃጠለም ይገባኛል ። አንተ ግን ማልቀስህ ለምን ነው ? " ጠየቀች የሳት ራቷ
ሻማው መለሰ ፦ " ኦ ውዴ ሆይ ፍቅር አልገባሽም በእውኑ ፥ አንቺ ስትርገብገቢ በነበልባሉ ፣ በውጋገኑ ሌት ሌቱን ስተዘዋወሪ ፤ እኔ በፅኑ እንደ ቆምኩ ነው ፥ ሙሉ በሙሉ እስክጠፋ ። ክንፎችሽ ተቃጥለው የከሰሙ እንድሆን ፤ ከአናቱ ጫፍ እስከ እግሩ ተቃጥሎ ሚጠፋውን እኔን ልብ አለማለትሽ "
ሌሊቱ ሳይገባደድ ፥ የሆነ ሰው መሬት ረገጥ የሻማውን ቅላጭ ፥ አንስቶ ሲጥለው ይታወቀኛል ፥ እያጉረመረመ
" Such is the end of love ! "
ሰዓዲ እንዲህ ይላሉ
Be cautious ; if thou goest to the sea , give thyself up the storm !
፫. ይቀጥላሉ ሰዓዲ
ልጁ ለፈጣሪው ፍቅር አደረ ሁሉን ነገር ሸሸ ፥ ወደ በረሃ ወጣም ፤ አባት በናፍቆት እንቅልፍ አጡ ፥ መመገብ አቆሙ ።
አንድ ሰው ቤታቸው መጣና ፥ ልጁ ከስደት በፊት ምን እንዳለው አስታወሳቸው ።
" ጓደኛዬ ለጓደኝነት ሲመርጠኝ ፥ ከርሱ ውጪ ያለውን መቀራረብ ጠላሁ ። ፈጣሪም ውበቱን ሲገልጥልኝ ከ'ርሱ ውጪ ያለው ነገር ሁሉ ቅዠት መሰለኝ "
የዚህ አይኖቶቹ
በመለኮታዊ እውቀት በረሃ ውስጥ ያለ ቅፍለት ፥ ለጉዞ 'ሚወጡት ናቸው (በፍቅር ስካር)
The Wander through the desert of Divine Knowledge with out a caravan.
[ምንጭ - የሰዓዲ - The Orchard of Sa'adi ]
፬.
እምብዛም ባታረካም ከ ፋሪዱዲን አታር [Fariduddin Attar] ተነስቼ በመልስኳት ግጥም ብንዘጋውስ(የተደገመባችሁ አውፍ በሉ)
"ሦስቱ ቢራቢሮዎች"
:
ወዲያ ጥግ ሻማ አለች ..
መቅረዝ እሳት አለ
.
ሻማዋ ትበራለች ..
ሶስት ቢራቢሮዎች
ከመቅረዙ ኃላ
ከሳቱ ነበልባል ፥ ውጋገኑን ርቀው
የሰው ልጅን ግብር ፥ ግለ ነፍሱን ወስደው
እሳቱን ያያሉ
:
አንድኛው
የፍሙን አውድማ
ሊዞር እንደ ካስማ
ይበራል
ይዞራል
ይከንፋል፤
የፍቅር ትርጉሙን
የፍቅር ሚስጥሩን
ከኔ ወዲያ ላሳር፥
እያለ ያወራል::
:
ሌላኛው
ሻማዋ ኣፋፍ ላይ
ሽራፊ ከክንፉ ፥ መስዋዕት አቀረበ
በስስ የሳት ላባ
የተነካች ክንፋን እያርገበገበ
እንዲ ሲል አሰበ
አውቃለሁ
የፍቅር እቅፋ ቃጠሎ እንዳለው
አውቃለሁ
የፍቅር አበባ እሾክ ያዘለ ነው
አውቃለሁ
የነበልባል ወጉን
የፍቅርን ገሞራ ፥ የፍቅር 'ሳት ጥጉን
:
ሦስተኛዋ ግን....
በሚነደው እሳት ፥ በሻማው ልቦና
ሁለ ሁለመነዋን
አፀደ ስጋዋን ፥ አሰጠመችና
ጠፋች
ከሰመች
የሚነደው እሳት
አንድዶ
ሰባብሮ
አክስሞ አስቀራት
እርሷ ማንንም አታውቅም
እርሷንም ማንም አያውቃት
ግና
ከ መቅረዙ ግርጌ ፥ አንድ ጥጉን ይዞ
ከጠፋ ገላዋ ፥ ካመዷ ላይ ቆሞ
ከቢራቢሮዋ ፥ ከርሷ ጋር የቀረ
አንድ እውነት ግን አለ
ፍቅር የተባለ፡፡
መልካም - ጁምዓ Sally Sufiza Eman Ab Meryem Ib
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
What will they say about my poetry
Who never touched my blood?
[P. Neruda]
ደሜን ያልቀመሱት
የፃፍኩትን ቅኔ ፥ እንዴት ነው 'ሚያወሱት ?
[ ፒ . ኔሩዳ ] - Repost
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
[I am only him - Mahmoud Darwish ]
ርቆ - ከ'ግሮቹ ዳና ጀርባ
ቀበሮ
የጨረቃን ብርሃን ዘንግ - ሊነክስ 'ሚያደባ
ርቆ - ከ'ግሮቹ ዳና ፊት
የከዋክብት መአት
ብርህን ሲያፈሱ - ከዛፎቹ አናት
እዚህ
ድንጋዮች - በቅርቡ
ከደም ስሮቻቸው - ደም 'ሚታለቡ ::
እናማ ያዘግማል አሁ��ም ያዘግማል
ቀልጦ እስኪጠፋ ..
ከእርምጃው መርጊያ - ከግሮቹ መድረሻ
ጥላው እስኪውጠው - በአፉ ጥልቅ ዋሻ
ግዴለም ፊቶቻችን - ለየቅል መልክ ይዋሱ
ማንም ሊሆን አይችል
እ'ሱን ልክ እንደኔ - እኔን ልክ እንደ 'ርሱ ::
እኔ እሱን ብቻ ነኝ !
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
Tumblr media
Brief Poems by Ono no Komachi
-
Without changing color
in the emptiness
of this world of ours,
the heart of man
fades like a flower.
-
Translated by Kenneth Rexroth and Ikuko Atsumi
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
Tumblr media
The autumn night
is long only in name—
We’ve done no more
than gaze at each other
and it’s already dawn.
~ Ono no Komachi
Translated by Jane Hirshfield and Mariko Arantani
Painting- Michel Rauscher
0 notes
selehadinali · 2 years
Text
፩ .
ሰዓዲ ይቀጥላሉ
"ከፀደይ ደመና አንዲት የዝናብ ጠብታ ወደ ምድር ወደቀች - ሰፊውን ባህር ስታይ በሀፍረት አቀረቀረች :: እንዲህም አለች :- " ባህሩ ሁሉ በሞላበት ፤ እኔ የት ነኝ ?በእርግጥም በህለውና የለሁም ልበል እንጂ ! "
በሀዘን ስታንጎራጉር በነበረበት ወቅት ነው አንድ የባህር ኦይስተር [Oyster] ወደ ሆዱ ውጦ ያስቀራት ፤ እጣ ክፍሏም ከትንሽ የዝናብ ጠብታ ወደ ክቡር የከበረ - ማዕድን ወደ ዕንቁነተ የቀየራት :: "
"ይሄው ነው" ይላሉ :- "አየህ ትሁት ነበረች ፥ ተከበረች ፤ ያለ መኖርን በር አንኳኳች ፥ ራሷን አሳነሰች ህልው የክቡራን ፅዋ - ተርታ ተቸራት :: "
፪.
አሁንም ሰዓዲ ይቀጥላሉ
ቀዘል አርሰላን ብርቱ የቤተ-መንግስት አጥር ነበረው - ቁመቱ ከ አልወንድ ተራራ የሚስተካከል [alofty mountain situated in Hamden , north-west of Isfahan] :: ከግንብ አጥሩ ውስጥ እንደ ሙሽራ ፀጉር በአፀደ - ፅጌያቱ ውስጥ እየተጠማዘዙ የሚዘልቁ ጎዳናውች ሞልተውታል ፤ በውስጧ ያሉ ኖሪዎቿ ሁሉ ያላንዳች ስጋት የተጠበቁ ነበሩ ::
ቀዘል በአንድ እለት - አንድ ጠቢብ መንገደኛ ያገኝና ይጠይቀዋል - ባንዳች የኩራት መንፈስ
" ከዚህ በፊት ይህን የመሰለ ብርቱ ግርማም የግንብ አጥር በተጏዝክበት ሁሉ አይተህ ታውቅ ይሆን ?"
" በእርግጥ ግሩም ነው !" ብሎ መለሰና :- " ነገር ግን አንዳች ብርታት እንደ ጎደለው አስባለሁ ፤ ካንተ በፊት የነብረው ንጉስ እጅ ላይ እንደ ነበር ሳስታውስ ፣ አሁንም ካንት በኇላ በሚነግሰው እጅ ላይ መውደቁን ሳስብ፣ ከዛም ደግሞ የነገሰው ንጉስ ከተስፋህ አፀድ ውስጥ ያሻውን ፍሬ ሲቢላ ይታየኝና - እውንትም አንዳች ጉልበት ፥ የሚመክትበት የተነሳው ነው እላለሁ :: "
In the estimation of the wise , the world is a false gem that passes each moment from one hand to another .
፫ .
አንድዎን የወሎ ሼኽ አንድ ያዲስ አበባ ሰው ሊኻድማቸው ወስዳቸው አሉ :: አሉ ነው መቼስ
ሁሉ ሁሉ ቀረበ ፣ ተበላም ተጠጣም :: ዱዓ ተያዘ ::
"ሼኾቹ እንግዲህ ያማረ ሀብት ፣ ያማረ መሬት ፣ ያማረ ቦታ ነው 'ምሻ በሉ ዱዓ ያርጉልኝ " አለ ከፊት ሆኖ እያያቸው
"እንግዲህ " አሉ :- " እንግዲህ አላህ ታንዱ ወስዶ ቲያበቃ ላንዱ ነው 'ሚሰጥና .. " እንዳሉ ሳያስጨርሳቸው
" ኧረ እነ ሸኽ እኔ የራሴን ነው 'ምፈልገው "
ቆጣ ብለው መለሱ :-
" ኧረግ ታያ ላንተ ተብሎ አዲስ መሬት አይዘረጋ !"
ምንጭ -Sa'adi collected works (Delphi classics)
ምርጥዬ ጁምዓ ብዘገይም !
0 notes