zeraseb
zeraseb
Untitled
6 posts
Don't wanna be here? Send us removal request.
zeraseb · 6 years ago
Text
Tumblr media
"ሰዉ" የለም ባገሩ (የብቻ እንጉርጉሮ)
°°°°°°°°°°°°°°°°°
ዓይንሽ ዕንባ አቅርሮ ያላየሁ መምሰሌ
መድማት መቁሰልሽን ያላየሁ መምሰሌ
ላትሞች መዳንሽን ያላየሁ መምሰሌ
ነፍሴ አትፍረጅብኝ ምኑን ከምን ላርገው
ዝምታዬ ሁሉ አደርገው ባጣ ነው።
እንደ ጭዳ ዶሮ ሰው በሰው ሲታረድ
ልክ እንደ ሲራራ ሰው በሰው ሲነገድ
ቀን ያነሳው ኀጥእ በምስኪን ሰው ሲፈርድ
ደም የጠማው ሰይጣን ሰው መስሎ ሰውን ሲያርድ
እያየሁ ያለየሁ መምሰል ሆነብኝ ግድ።
ሰው ነኝ ብሎ የሚምል የሰውነት ዕዳ
ከሰውነት ወርዶ በሰው የሚነዳ
ገዳይና ሟቾች እኩል ሰዎች ቢሉኝ
ጥርጣሬ ገባው ልቤ አላምን አለኝ፤
ሰው እንዲህ መክፋቱ እጅጉን ሰቀቀኝ
ካውሬነት መውረዱን ዓይኔ ስላሳየኝ።
ሰዉ ከእንስሳ ሲያንስ ዘመን ስላሳየኝ።
እብከነከናለሁ...
እንከላወሳለሁ ሃዘኔን ቀብሬ
ሰውነት የራቀው ሰው አብቅላ ሀገሬ።
አኬልዳማ ሆና ፍጹም የደም መሬት
አልመጻደቅም ሰው ክቡር በማለት
ከሰውም መካከል አጋንንት አለበት።
ከሰይጣን የከፋ የሚብስ ከእስስት።
...
ሀገር እያነባች ያላየሁ መምሰሌ
መቁሰሏን መድማቷን ያላየሁ መምሰሌ
ስትሞት ስታጣጥር ያላየሁ መምሰሌ
አስችሎኝ አይደለም በዝምታ የማልፈው
ግራ ተጋብቼ አደርገው ባጣ ነው።
ደረቴን ደቃሁት ልክ እንደ ከበሮ
በዘግናኝ ግድያ ልብና አንጀቴ አርሮ።
ክራሬን ልደርድር ዋሽንቴንም ልንፋ
የነፍሴን ስቅዛት ይዞልኝ ቢጠፋ።
ሀገሬ ዜማ አላት ባለድንቅ ቅኝት
አንቺሆዬ፣ አንባሰል ትዝታ የሚሉት።
አንቺሆዬ ለኔ የሰርግና ያዘን
በሆነው ባየነው ሲደፍቀን ሰቀቀን፤
ደረቴን ልደርድር በትዝታ ቅኝት
ማረፍ እንዴት ሊቻል ልቤን ሀዘን በልቶት።
አካሌን ሰቀቀን እንደ ሲዖል ዉጦት።
ሰው ልክ እንደ ሙጃ፣
እንደማይፈለግ አረም አራሙቻ
ሲቀጠፍ፣ ሲነቀል ሲጣል ከስርቻ
አካሉ ሲበለት እንደ ሥጋ ቅርጫ
ይሄንን ባልሰማ ሊያልፉ ከደፈሩ
ከህይወት አብልጠው
ከህይወት አብልጠው ከሞት ጋር ካበሩ
ገዳይ፣ ሟችና አልቃሽ ከንቱ ፎካሪ እንጂ
ለነፍስ ለህይወት ፍጹም የወገነ "ሰው" የለም ባገሩ።
ዘርዓሰብ ሣጌጥ
ተጻፈ 22 ጥቅምት 2012 ዓ.ም
"ሰው" - 'ሰው የጠፋ ዕለት ሰው ሆኖ የተገኘ ሰው' ተብሎ ይያዝልኝ።
0 notes
zeraseb · 6 years ago
Text
Tumblr media
0 notes
zeraseb · 6 years ago
Photo
Tumblr media
0 notes
zeraseb · 6 years ago
Text
Tumblr media
እንኳን ከኔ ሰራሽ
°°°
አቤት ውበት! አቤት ማማር
እንደ አበባ ልክ እንደ ማር።
ወለላ ነሽ፣ ጥዑም ጣፋጭ
ታየኝ ውበት ተርፎሽ ሲረጭ።
ሺ ዓይና እንጀራ ይቅርብኝ
ያንቺ ዓይን ነው የሚያጠግበኝ
ካይኖችሽ ስር ተሰይሜ
ሲያስተዉሉኝ እያየሁኝ
ኮከብ እንጂ የማለዳ
ዓይኗ አይደለም ብዬ ማልኩኝ።
ከንፈርሽ ላይ ትክ ብዬ፣ አተኩሬ ስመረምር
ግር ይለኛል፣ አበባ ነው ወይስ ከንፈር?
የምን ከንፈር? አበባ ነው።
ንብ ያድርገኝ እንድቀስመው።
የለም የለም ይህ ቅጥፈት ነው።
አምላኳ ሆይ ይቅር በለኝ
ለጌጥም ከበቃት ነው
እንኳን ከንፈሯን ሊመስለኝ።
ካይኖችሽ ስር ተሰይሜ
ቀና እንዳልል ዓይንሽ ገታኝ
ፍቅርሽ ከአድማስ እራቀብኝ።
ከሁለንታ ረቀቀብኝ።
አቅም አጣሁ ለማቀርቀር
አነሁልሎኝ ውብ ማር ከንፍር።
የኔ ልዩ፣ ውብ ስጦታ
ቃላት አጣሁ ምን ልበልሽ?
አትሰልቺኝ ደጋግሜ ውብ ነሽ ስልሽ።
እራሴንም ይሄን ያህል የወደድኩት አይምሰልሽ
ብቻ እግዜሩን እግዜር ይስጠው
አንቺን መርጦ ከኔ ሰራሽ።
ከኔ ሰርቶም ለኔ አረገሽ።
የኔ ልዩ፣ አንቺ ማለት ውብም ቆንጆም ሙሉ ሴት ነሽ
አድማስ አልፎ የሚሻገር የዘላለም ሚዛኔ ነሽ።
©ዘርዓሰብ ሣጌጥ
፫\፪\፪፳፩፪ ዓ.ም
0 notes
zeraseb · 6 years ago
Text
Tumblr media
እንኳን ከኔ ሰራሽ
°°°
አቤት ውበት! አቤት ማማር
እንደ አበባ ልክ እንደ ማር።
ወለላ ነሽ፣ ጥዑም ጣፋጭ
ታየኝ ውበት ተርፎሽ ሲረጭ።
ሺ ዓይና እንጀራ ይቅርብኝ
ያንቺ ዓይን ነው የሚያጠግበኝ
ካይኖችሽ ስር ተሰይሜ
ሲያስተዉሉኝ እያየሁኝ
ኮከብ እንጂ የማለዳ
ዓይኗ አይደለም ብዬ ማልኩኝ።
ከንፈርሽ ላይ ትክ ብዬ፣ አተኩሬ ስመረምር
ግር ይለኛል፣ አበባ ነው ወይስ ከንፈር?
የምን ከንፈር? አበባ ነው።
ንብ ያድርገኝ እንድቀስመው።
የለም የለም ይህ ቅጥፈት ነው።
አምላኳ ሆይ ይቅር በለኝ
ለጌጥም ከበቃት ነው
እንኳን ከንፈሯን ሊመስለኝ።
ካይኖችሽ ስር ተሰይሜ
ቀና እንዳልል ዓይንሽ ገታኝ
ፍቅርሽ ከአድማስ እራቀብኝ።
ከሁለንታ ረቀቀብኝ።
አቅም አጣሁ ለማቀርቀር
አነሁልሎኝ ውብ ማር ከንፍር።
የኔ ልዩ፣ ውብ ስጦታ
ቃላት አጣሁ ምን ልበልሽ?
አትሰልቺኝ ደጋግሜ ውብ ነሽ ስልሽ።
እራሴንም ይሄን ያህል የወደድኩት አይምሰልሽ
ብቻ እግዜሩን እግዜር ይስጠው
አንቺን መርጦ ከኔ ሰራሽ።
ከኔ ሰርቶም ለኔ አረገሽ።
የኔ ልዩ፣ አንቺ ማለት ውብም ቆንጆም ሙሉ ሴት ነሽ
አድማስ አልፎ የሚሻገር የዘላለም ሚዛኔ ነሽ።
©ዘርዓሰብ ሣጌጥ
፫\፪\፪፳፩፪ ዓ.ም
0 notes
zeraseb · 6 years ago
Text
Tumblr media
የማምነውን ፍቅር
°°°°°
የነፍሴን ሰው መሻት ካወቅኩኝ ጀምሮ
የሴትን ጸጋነት ካመንኩኝ ጀምሮ
ይሄው አስሳለሁ
ሰው እፈልጋለሁ።
የስሜቴን ንግሥት የውስጥያዬን ልክ
አላገኘኋትም ብፈልግ፣ ብፈልግ።
ይሰምራል እያልኩኝ፣ ይዣለሁ ፍለጋ
ዘመናት አለፉ፣ ብቻዬን አምሽቼ ብቻዬን ሳነጋ።
ባየኋት እንስት ውስጥ ሳሰላው ምኞቴን
ምኞቴ ተንዶ፣ በቆሰለ ልቤ የምቀር ሌጣዬን
በታየኋት ሴት ውስጥ የወጠንኩት ፍቅር
አቁስላኝ ወይ ቆስላ ትርፉ ያው መቃቃር።
ላየችኝ አልሆናት፣ ያየኋት አትሆነኝ
መፈቃቀር ማለት ይቻል አመስል አለኝ።
የማምነውን ፍቅር ልኖረው ተሳነኝ
የፍቅር አምላክ ሆይ ባክህ ተለመነኝ።
©ዘርዓሰብ ሣጌጥ
፪\፪\፪፳፩፪ ዓ.ም
1 note · View note